ከምግብ ጋር የተያያዙ ሙዕጂዛዎች
በኸንደቅ የምግብ መባረክ
ጃቢር ያዘጋጀው ጥቂት ምግብ ጉድጓዱን ይቆፍር የነበረውን ሠራዊት በሙሉ አጠገበ።
የምግብ መባረክና መብዛት።
ከምግብ ጋር የተያያዙ ሙዕጂዛዎች
ጃቢር ያዘጋጀው ጥቂት ምግብ ጉድጓዱን ይቆፍር የነበረውን ሠራዊት በሙሉ አጠገበ።
ከምግብ ጋር የተያያዙ ሙዕጂዛዎች
በልጅነታቸው ከአጎታቸው ከአቡ ጧሊብና ከቤተሰቡ ጋር ሲመገቡ ሁሉም ይጠግቡና ይረኩ ነበር፤ እርሳቸው በሌሉበት ሲበሉ ግን አይጠግቡም ነበር።
ከምግብ ጋር የተያያዙ ሙዕጂዛዎች
በሒራ ለእርሳቸው ብቻ ካመጣው ጥቂት ምግብ «ቢስሚላህ፣ ብሉ» ባሉ ጊዜ በቅፍለቱ ያሉ መቶ ሰባ ሰዎች እስኪጠግቡ ድረስ በሉ።
ከምግብ ጋር የተያያዙ ሙዕጂዛዎች
ከሻም ጉዞ የተመለሰው መይሰራ ለኸዲጃ መነኩሴው «ከዒሳ በኋላ ከዚህ ዛፍ ሥር ከነቢይ በቀር ማንም አይቀመጥም» እንዳለና ከእርሳቸው ጋር የበሉት ምግብ ሁልጊዜ እንደሚተርፍ ተረከላት፤ ኸዲጃ ይህን ለመፈተን አንድ ሳሕን ተምር አስመጥታ እህቷን ሃላንና ራሷን ጠራች፤ ሁሉም ቢጠግቡም ተምሩ ፈጽሞ አልጎደለም።
ከምግብ ጋር የተያያዙ ሙዕጂዛዎች
የቅርብ ዘመዶቻቸውን በጋበዙበት ግብዣ አንድ ታፋ ሥጋና አንድ ዕቃ ወተት 40 ሰዎችን አጠገበ።
ከምግብ ጋር የተያያዙ ሙዕጂዛዎች
ቁረይሽ በሺዕብ ከበው የምግብ መግቢያን በዘጉባቸው ዓመታት ለእርሳቸውና ከእርሳቸው ጋር ላሉት ከመንና ከሰልዋ የተሻለ ሲሳይ መጣላቸው፤ ሁሉም የተመኘውን ምግብ አገኘ፤ እጅግ ያማሩ ልብሶችም ተለበሱላቸው።
ከምግብ ጋር የተያያዙ ሙዕጂዛዎች
በኡሙ መዕበድ ድንኳን የነበረችውን ወተት የሌላትና የከሳች በግ ጡቷን ባሻሹ ጊዜ ሁሉንም የሚያጠግብ ወተት ሰጠች።
ከምግብ ጋር የተያያዙ ሙዕጂዛዎች
በመንገድ ላይ ያገኙት ባሪያ እረኛ ገና ካልወለደችው በግ ወተት አለቡ።
ከምግብ ጋር የተያያዙ ሙዕጂዛዎች
ከአቡበክር ጋር ከመካ ከወጡ በኋላ ባለፉበት የዐረብ ሰፈር ብቻዋን የምትኖር ሴት አሮጌና ወተቷ የደረቀ በግ ጡቷን አሻሽተው ዕቃውን የሚሞላ ወተት አለቡ፤ ሴቲቱ፣ ልጇ እና አቡበክር ጠጡ፤ ሴቲቱ «ሙባረክ» (የተባረከው) ብላ ታስታውሳቸው ነበር፤ መንጋዋ በዛ፤ በኋላም ወደ መዲና መጥታ ሙስሊም ሆነች።
ከምግብ ጋር የተያያዙ ሙዕጂዛዎች
አቡ ኡማማ አስዐድ ኢብኑ ዙራራ በየቀኑ በቀትርና በምሽት ከሚልከው አንድ ሳሕን ፍትፍት ከአጠገባቸው ካሉት ጋር በሉ፤ ሁሉም ጠገቡ፤ ሳሕኑም እንዳለ ተመለሰ።
ከምግብ ጋር የተያያዙ ሙዕጂዛዎች
በዐሊይ የሠርግ ግብዣ ላይ ጥቂቱ ምግብ ለብዙ ሰዎች በቃ።